Twitter Like

Aug 5, 2013

Ethiopian job interviews
የስራቃለመጠይቆች-የተለመዱ የስራ ቃለ መጠይቆችና መልሶቻቸዉ
ምንም እንኯን በእርግጠኝነት በቃለመጠይቅ ወቅት የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ማወቅ ባይቻልም ብዙዉን ጊዜ የሚጠየቁ ቃለመይቆችን በመመልከት መዘጋጀት አለብን:: አነዚህን ጥያቄዎች ማወቅ በቃለመጠይቁ ወቅት ራሳችንን ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ዉጤቱን ለመቆጣጠርም ይረዳናል::

የተለመዱ የስራ ቃለ መጠይቆች

ምንም አይነት የትምህርት ክፍል ብንሆን ጠያቂዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች ማንሳታቸዉ አይቀሬ ነዉ::

1. ስለ ራስህ/ሽ ልትነግረኝ/ልትነግሪኝ ትችላለህ/ትችያለሽ?

ይህ ጥያቄ በጣም የተለመደና ብዙዎች የሚጠሉት ጥያቄ ነዉ በተለየ ሁኔታም ይህን ጥያቄ የቃለመጠይቁ መክፈቻ አድርገዉም ይጠቀሙበታል:: የዚህ ጥያቄ መልስም ቀጣሪዉ ስለ ማንነታችንና ብቃታችን ፍንጭ ይሠጣል::
መልሱን ስንመልስም አጠር ያለ የህይወት ታሪክ እዉቀትና የስራልምድ ማቅረብ ይጠበቅብናል::

2. እዚህድርጅት ለመቀጠር ምን አነሳሳክ/ሽ?

ምንም እኯን እውነታዉ እርሶ ስራዉን የሚፈልጉት ገንዘብ ለማግኘት ቢሆንም እንዲህ አይነት መልስ መመለስ ግን ተገቢ አይሆንም:: ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ስለ ድርጅቱ አንዳንድ መረጃዎችን መሰብሰብና ድርጅቱን ለምን እንደምናደንቀዉ አሳማኝ ምክንያት ይዞ መቅረብ ይኖርብናል::

3. ለምን እንቅጠርህ/ሽ?

ይህ ወሳኝ ከሆኑት ጥያቄዎች አንዱ ሲሆን እርሶም ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ሊኖሮት ይገባል::

0 comments:

Post a Comment